የሜትር ታክሲዎች ለዲያስፖራ አባላት የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ተስማሙ

የሜትር ታክሲዎች ለዲያስፖራ አባላት የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ተስማሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት፣ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ ተቀብለው ለገና በዓል ወደ አገር ቤት ለሚመጡ የዲያስፖራ አባለት ከዛሬ ጀምሮ የነጻ የትራንስፖር አገልግሎት ለመስጠት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በዛሬው እለት በኤሊያና ሆቴል ከታክሲ ማህበራት አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ወቅት የማህበራቱ ተወካዮች እንዳሉት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ የዲያስፖራ አባላት ከአየር ማረፊያ እስከ መዳረሻቸው ድረስ የነጻ የትራንስፖር አገልግሎት ለመስጠት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱ የገና በዓል እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ መስማማታቸውን የገለጹትም ከ45 በላይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት መሆናቸውም ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY