ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ተጨማሪ በጀቱ ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፡፡
ተጨማሪ በጀቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፣ መንግስት በሚሰበስበው ገቢ አሁን ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም የተጨማሪ ወጪ ፍላጎትን በበጀት ሽግሽግ ማስተናገድ አዳጋች በመሆኑ ነው፡፡
የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንደ ጸደቀ በቀጥታ ስራ ላይ እንደሚውል ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

























