ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ወሎ እንዲሁም የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ላንድክሩዘር መኪና ተበረከተላቸው።
የመኪና ስጦታውን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አስረክበዋቸዋል።
አሸባሪው ቡድን ወልድያ ከተማን በወረረ ጌዜ ከባድ ዘረፋ እና ውድመት በፈጸመበት ወቅት የብጹዕ አቡነ ኤርሚያስን መኪናም መዝረፉ ይታወሳል።
ዛሬ በስጦታ የተረከቡት ተሽከርካሪም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል። አቡነ ኤርሚያስም መንግሥት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል ።