ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ...

ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ።

ዐቃቤ ህግ አሉኝ ብሎ በክሱ ላይ ከጠቀሳቸው ምስክሮች ውስጥ 6 ምስክሮን ያሰማ ሲሆን 7ኛ ምስክር በተደጋጋሚ በተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ በፖሊስ ታስሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥም ትዕዛዙ ሳይፈጸም፤ ምስክሩም ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡

ችሎቱም በተደጋጋሚ ቀጠሮ ላልቀረበው ምስክር በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲል ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 25 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን
በዚሁም መሰረት ዐቃቤ ሕግ እስካሁን ባሰማኋው ምስክሮች እና ባቀርብኳቸው ማስረጃዎች መሰረት ብይን ይሰጥ ብሎ መጠየቁን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY