ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የ34 አመቱ ወጣት ሎታታ ላክስ በደቡብ አፍሪካ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተሰሚነቱ እየጨመረ የመጣ የማህበረሰብ መሪ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ላክስ በሚኖርበት በሚኖርበት ሱዌቶ “ሶዌቶ ፓርላማ” የተሰኘ የወጣቶች ህብረትን በመፍጠር ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን ሰፊ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል።
ወጣቱ የመሰረተው እና የሚመራው የሶዌቶ ፓርላመንት ከፓለቲካ ፣ሃይማኖት እና ዘር ነፃ የሆነ ህብረት ነው።
ለፍትህ እና እኩል ተጠቃሚነት በሚያደርጋቸው ትግሎች በርካቶችን እያሰከተለ አሁን ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ደቡብ አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆኗል።
ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርስም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተወካይ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እና የወጣቶች ፌዴሬሽን ም/ ኘሬዝዳንት ፅጌረዳ ዘውዱ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮኘላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውለታል።
ላክስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ጠንቅቄ አውቃለሁ ብሏል። የመምጣቱንም ምክኒያት ሲያስረዳ ወጣት እንደመሆኔ ወጣቱን የኢትዮጵያ መሪ መደገፍ አለብኝ፤ የመጣሁበት አንዱ ምክኒያትም እርሱን ለመደገፍ ነው” ሲል ተናግሯል።
በደቡብ አፍሪካ ተካሂዶ በነበረው nomore ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድጋፉን የሰጠ ሲሆን አፍሪካውያን ኢትዮጵያን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
ከውስጥ እና ከውጭ ሃይሎች አህጉሪቱ የሚገጥማትን ፈተና ወጣት አፍሪካውያን በጋራ መታገል አለብን” ብሏል ዛሬም በሰጠው መግለጫ ላይ።
ኢትዮጵያ የመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ መሆኗን ያስታወሰ ሲሆን ለአፍሪካ በተለይም ለሃገሩ ደቡብ አፍሪካ የነፃነት እና የፀረ አፓርታይድ ትግል ያደረገችው ድጋፍ በታሪክ ልዩ ስፍራ እንደሚሰጠው ተናግሯል