ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ነገ ታኅሣሥ 28 ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይጠበቃል። በድርድር ስም አሸባሪውን ትሕነግ ለማዳን እየጣረች የምትገኘው አሜሪካ ባለሥልጣን ይህንኑ ተልዕኮ ይዘው በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል።
ሆኖም መንግሥት አሁን ላይ ስለድርድር ያለው ነገር አለመኖሩንና ድርድር ቢኖር እንኳን የትኛውም መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው አካል ቅድመ ሁኔታን እንደማይቀበል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰሞኑ ከሆርን ሪቪው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ማሳወቃቸው ይሚታወስ ሲሆን ፌልትማን ነገ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር “ስለ ሰላም ድርድር ጉዳይ ለመነጋገር” እንደሆነ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መግለፃቸውን የውጭ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት።