ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ላይ የፌደራል ተቋማትን የ100 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የተለያዩ ሚኒስትሮች የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከሌሎች ሚኒስትሮች ጋር በመሆን ግንባታው በመፋጠን ላይ ያለውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ዛሬ የህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነችው ጉባ የተጀመረው የፌደራል ተቋማትን የ100 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የሁሉንም ተቋማት አፈፃፀም ፈትሾ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል ተብሏል።