ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ጠቁመዋል።
አሜሪካ ኢትዮጵያን የቀረጥና ኮታ ነፃ ገበያ (አግዋ) አባልነት እንዳገደች ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መፈረማቸው የሚታወስ ሲሆን
ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም ውይይቱ ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ሁለታችንም ተስማምተናል ብለዋል።