በአዲስ አበባ በ8 ቢሊዮን ብር በጀት የ5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ...

በአዲስ አበባ በ8 ቢሊዮን ብር በጀት የ5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ ፐሮጀክት ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ለሚገነቡ 10 ሺህ ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በምዕራፍ 1 ፕሮጀክት የሚገነቡ የ5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳናች አቤቤ አስጀምረዋል።

ዛሬ ግንባታ ለማካሄድ የተጀመረው መሬት በህገ ወጥነት ተይዞ የነበረ ወደ መሬት ባንክ በማስገባት መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚገነባቸው የተጋጋጠሚ ቤቶቹ በአንድ ዓመት ተገንብተዉ ለማጠናቀቅ እንደሚሠራ ተነግሯል፡፡
የሚገነቡት ቤቶች ባለ 4 እና ባለ 10 ወለል ሕንጻዎች ሲሆኑ ቤቶቹ ተገንብተው ሲጠራቀቁ በከተማ ደረጃ የተያዘውን ቤቶችን ለዜጎች ተደራሽ የማድረግ ዕቅድ በከፊል የሚያሳካ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

ፕሮጀክቱ የተሻለ የግንባታ አሠራር ቴክኖሎጂዎችን ከማስፋፋት በተጨማሪ በርካታ የሥራ ዕድሎችን የመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
የአ/አበባ ቤቶች አስተዳደር በተለይም በቅርቡ በብድር ቦንድ ከሚያስገነባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ጎን ለጎን የተለያዩ የቤት የፋይናንሲንግ አማራጮችን በማጥናትና አለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ትግበራ ለማስገባት እየሰራሁ ነዉ በሏል።

ከባለፈው ትምህርት ተወሶዶ በአጭር ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ቤቶቹ በመገንባት የከተሞችን ነዋሪዎች የቤት ጥያቄ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ማስጀመርያ ላይ ገልፀዋል።

ይህም በተለይ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት በቤቶቹ ምክንያት የተከማቸ የ54 ቢሊዮን ብር እዳ መክፈል ፈተና እንደነበርም አንስተዋል፡፡

LEAVE A REPLY