ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አስፈላጊ ግብዓቶችን አሟልቶ መደበኛ ስራዉ መመለሱን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከአገልግሎት ዉጪ ሆነው የነበሩ መሰረተ ልማቶችና የወደብ ማሽነሪዎችን በመጠገን እንዲሁም የሰው ኃይል፣ የቢሮ መገልገያዎችና አስፈላጊ ግብዓቶችን በማደራጀት ወደ ስራ መመለሱን ነው የገለጸው።
ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. የሕወሓት ቡድን የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናልን ማውደሙን እና የደንበኞችን ንብረት የያዙ 251 ኮንቴይነሮችን መዝረፉን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን
የኮምቦልቻ ወደብ ወደ ስራ መመለስ በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎች የጥሬ እቃዎችና የግብዓት ፍላጎታቸውን በፍጥነት ለማሟላት ያግዛል ተብሏል።
የአገልግሎት ድርጅቱ አክሎም ከእዚህ ቀደም በወደቡ ሲገለገሉ የነበሩም ሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ወደ ኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል እቃዎችን ማስመጣት እንደሚችሉ አስታዉቋል።