ኦባሳንጆ ትናንት በመቀለ ከህወሃት መሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተገለጸ

ኦባሳንጆ ትናንት በመቀለ ከህወሃት መሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ አቅንተው ከህወሃት አመራሮች ጋር መነጋገራቸውን የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።

ቃል አቀባዩ በትዊተር ገጻቸው፣ ኦባሳንጆ በአፍሪካ ቀንድ ላጋጠሙ ችግሮች ሰላማዊ መፍትሔን ያፈላልጉ ዘንድ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጋር በተያያዘ መቀሌ መገኘታቸውን አስፍረዋል።

አክለውምከትግራይ መሪ ጋር መልካም ውይይት ስለማድረጋቸው ተስፋ አድርጋለሁ ሲሉ ገልፀዋል።
ከጥቅምት ወር ወዲህ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት በተባባሰበት ጊዜ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ቢያንስ ለሁለት ጊዜያት ያህል ወደ ትግራይ ተጉዘው ከህወሃት መሪዎች ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ይታወሳል።
ነገር ግን ስለአሁኑ ጉዟቸው ከህወሃቱ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ውጭ የገለጸ አካል የለም።

የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕከተኛው ከትናንቱ ውይይታቸው በኋላ ከመቀለ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ጌታቸው ረዳ ጨምረው አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY