ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሀገራቸው አሜሪካ ትኩረቷ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜው ማምጣት ነው ብለዋል።
ሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት የተንሰራፋውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ረገጣና ስቃይ ለማስቆም ከሁሉ የተሻለው መንገድ ጦርነቱ መቋጫ የሚያገኝበትን መንገድ መፈለግ እንደሆነ ኔድ ፕራንስ ተናግረዋል።
ለዚህ አሜሪካ ልዩ ትኩረት ለሰጠችው ጉዳይ ጠንካራ ዴፕሎማሲ እየተከተለች ነው ብለዋል።
ኔድ ፕራስ አክለውም ጠንካራ ዴፕሎማሲ እየተከተልን ነው። በመሪዎች ደረጃ የተካሄደው የስልክ ውይይት የዚህ አካል ነበር። አምባሳደር ፌልትማን እና የአሁኑ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ስታርፊልድ በዚህ ውስጥ በጥልቀት ተሰማርተዋል።
ከቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉ ኦባሳንጆ ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ነን ሲሉ የገለፁ ሲሆን ቃል አቀባዩ ፕራስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጋር የመነጋገር እድል እንዳገኙ አንስተዋል ንግግሩ አንዱ የዲፕሎማሲው አካል ነው ብለዋል።
ኔድ ፕራስ አሁን ያለው ሁኔታ በግጭት ውስጥ ላሉት ወገኖች መልካም እምነትን ለማሳየት እድል ይሰጣል ብለን እናምናለን ያሉ ሲሆን ውጊያ አቁመው ወደ ድርድር ጠረጴዛ ሊመጡ ይህ ደግሞ ግጭቱ እንዲዘጋ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ማመልከታቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።