ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጉዳይ የግላቸውን አቋም እንዳያንጸባርቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጉዳይ የግላቸውን አቋም እንዳያንጸባርቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዋና ዳይሬክተሩ ትናንትና ረቡዕ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ላሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ አግዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በራሱ ዜጎች ላይ ምግብ፣ መድሃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ድጋፎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ሲሉም ነበር ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
ይህን ተከትሎ በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ፖለቲካዊ ውግንና አላቸው ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁና ገለልተኛ እንዲሆኑ ጠይቋል፡፡

ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት የጤና ተቋማት ሲወድሙ ምንም አላለም በሚል የዓለም ጤና ድርጅትን መውቀሷ የሚታወስ ሲሆን የተሰጣቸውን ዓለም አቀፋዊ ሚና ከመወጣት ይልቅ ከፖለቲካዊ እና ግለሰባዊ ፍላጎት የመነጨ ውግንናቸውን እያንጸባረቁ ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ የተመድ ኤጀንሲዎች ስራም በዚሁ ምክንያት እየተስተጓጎለ ይገኛል ብሏል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ የትኞቹም ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁም ነው በተመድ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ጽ/ቤት የጠየቀው፡፡

LEAVE A REPLY