ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠመቸው የጤና እክል ምክንያት ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገለጸ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ከክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሊነጋገሩበት ለዛሬ ጥር 6 ቀጠሮ መያዙን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው፣ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።