የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ መነጋገራቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ልዩ መልዕከተኛው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ እና በሁሉም አካላት መካከል ውይይት እንዲፈጠር ለማበረታታት የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።

ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በአፍሪካ መሪነት ለሚደረገው የሽምግልና ጥረቶች ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ እና ካናዳ በዚህ ረገድ የአፍሪካ ህብረትን ስራ ለመደገፍ ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች ያለ ምንም እንቅፋት ሰብዓዊ ዕርዳታ በማድረስ ሂደት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ሰላማዊ ዜጎችን መጠበቅ፣ ህይወት ማዳንና የሰብአዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY