የአፍሪካ ሕብረቱ ሰብሰባ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው ተባለ

የአፍሪካ ሕብረቱ ሰብሰባ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ካከናወነችው የሕግ ማስከበር ተግባር ጋር ተያይዞ አገሪቷ ውስጥ ሰላም የለም፤ አለመረጋጋት ተበራክቷል፤ ስለሆነም ስብሰባውን ማካሄድ አይቻልም ሲሉ ለነበሩ አካላት ተገቢ መልስ የሚሰጥ ነው የሉ ሲሆን ስብሰባው በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት የለም በሚል አጀንዳቸውን ለማራገብ የሞከሩ አካላትን ዓላማ ያከሸፈ ነው ብለዋል።

በተጨማሪ አንዳንዶች እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ ዜጎቻቸው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፤ ዜጎቻቸውንም ያስወጡ አገራት አሉ። እነዚህ ወገኖች ተግባራቸው ትክክል እንዳልሆነና ኢትዮጵያ አሁንም በአንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ውስጥ እንደምትገኝ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ምንም እንኳን በተወሰነው የኢትዮጵያ ክፍል ግጭት ቢኖርም አብዛኛውም የአገሪቷ ክፍል በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ያሉት አምባሳደር ዲና፤ ኢትዮጵያም የተጋረጡባትን ችግሮች እያሸነፈች የሄደች አገር ነች ብለዋል።
አሁንም የኅብረቱ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ እንደከዚህ ቀደሙ ሊካሄድ ዝግጅት መደረጉ ኢትዮጵያ የሚመጡባትን ፈተናዎች ሁሉ እያሸነፈች መቀጠል እንደምትችል የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በኮቪድ ወረርሽኝ መስፋፋት ምክንያት የአፍሪካ ኅብረትን ስብሰባ በአካል ተገኝቶ ማድረግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ያ ጊዜ አልፎ አሁን ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባው በመሪዎች ደረጃም ጭምር እንዲካሄድ መወሰኑ በኢኮኖሚውም ረገድ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በተለይ የትራንስፖርት፣ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉም የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በአጠቃላይ ስብሰባው የአገርን ገጽታ ከመገንባት አኳያ የሚኖረው ትሩፋት ትልቅ ነው። በተጨማሪም ስብሰባው መካሄዱ የፓንአፍሪካኒዝምን መንፈስ እንደሚያጠናክረው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያውያንና የአፍሪካ ዝርያ ያላቸው ሰዎች እያደረጉ ላለው የበቃ እንቅስቃሴ ተጨማሪ እስትንፋስ የሚሰጥ ስብሰባ ይሆናል። መሪዎች የአፍሪካን አጀንዳ አውጥተው ስለአፍሪካ የሚወያዩበት በመሆኑ የበቃ እንቅስቃሴም ተጨማሪ ሞገስ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ስብሰባው እንዲካሄድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩልም ከፍተኛ የማግባባትና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች ሲካሄዱ እንደነበር ያስታወሱት አምባሳደር ዲና፤ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በየዘርፉ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች 24 ሰዓት በመስራት የመስተንግዶና የተለያዩ ሁነቶች የሚስተናገዱባቸውን ዝግጅቶችን እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደተለመደው በእንግዳ አክባሪነቱ ለስብሰባው የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

35ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ የመሪዎች መደበኛ ስብሰባ ከጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

LEAVE A REPLY