ሕወሓት በአፋር ጦርነት በመከፈቱ የትግራይን የሚገባውን የሰብኣዊ ዕርዳታ ማስተጓጎሉ ተገለጸ

ሕወሓት በአፋር ጦርነት በመከፈቱ የትግራይን የሚገባውን የሰብኣዊ ዕርዳታ ማስተጓጎሉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር አብአላ በከፈተው ጦርነት ወደ ትግራይ ክልል የሚገባውን የሰብኣዊ ዕርዳታ ማስተጓጎሉን የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደበበ ዘውዴ ለኢፕድ እንደገለጹት አሸባሪው ሕወሓት በአፋር አብአላ መስመር በከፈተው ጦርነት የተነሳ በዋነኛው የትግራይ ክልል ሰብኣዊ ድጋፍ የተሽከርካሪዎች መተላለፊያ መስመር ላይ እክል ተፈጥሯል።

ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የሰብኣዊ ዕርዳታ ዋነኛ መተላለፊያ በአፋር ክልል ሰመራ አድርጎ በአብአላ የሚገባው መስመር መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ የሽብር ቡድኑ በዚህ መተላለፊያ ላይ ጥቃት በመክፈቱ መስተጓጎሎች እየተፈጠሩ ነው ብለዋል።

ይህን በማድረጉም መንግሥት ወደ ትግራይ የሚገባውን መስመር ዘጋ በማለት፤ ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የውሸት ክሱን ለማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY