የተመድ ዋና ጸሀፊ ከአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ኦሊሲንጎ ኦቦሳንጆ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ...

የተመድ ዋና ጸሀፊ ከአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ኦሊሲንጎ ኦቦሳንጆ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ተማከሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬዝ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ክቡር ኦሊሲንጎ ኦቦሳንጆ በኢትዮጵያ ባለው ግጭት ዙሪያ በመቀሌና በአዲስ አበባ ያደረጉትን ግብኝት ተከትሎ በዛሬው እለት የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ ሲሉ አስተውቀዋል።

ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡ ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ግጭቱን ለማስወገድ እያደረጉ ስላሉት ጥረት ገለጻ አድርገውልኛል” ያሉት ዋና ጸሀፊው ግጭቱና ጥቃቱ እንዲያበቃ አሁን ፖሊካዊና ዲፕሎማሲያዊ እልባት ለመስጠት የሚያስችል ትክክለኛ እድልና አጋጣሚ ስለመኖሩ ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ጉተሬዥ ከአንድ ዓመት በላይ በመላው ኢትዮጵያና በአካባቢው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት ከዳረገው ግጭት በኋላ አሁን ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡

በአንዳንድ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች አሁንም የሚካሄደው ውጊያ ለሰላም ሂደቱ መራር ፈተና መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሀፊው በሁሉም ወገኖች ዘንድ መተማመን የሚፈጥሩ ጠንካራ እምርጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ጎተሬዝ አሁንም ሰላምን ለማስፈን ትክክለኛው አቅጣጫ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ማቆሙ ያላባቸው መሆኑን ያቀረብኩትን ጥሬዬን እንደገና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የሚመራ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ የሰላም የደህንነትና የእርቅ ሂደትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሁሉም ወገኖች ለሰላሙ ሂደት በቅንነትና በቁርጠኝነት እንዲሳተፉ የሚያደርገውን ጥረት መቀጠል አለበት ብለዋል።

LEAVE A REPLY