በዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ መንግሥት ያቀረበውን አቤቱታ ድርጅቱ ላለማየት ወሰነ

በዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ መንግሥት ያቀረበውን አቤቱታ ድርጅቱ ላለማየት ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ ያቀረበውን አቤቱታ ላለማየት መወሰኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ አልወያይበትም ብሎ ወደ ጎን የገፋው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴዎድሮስ የአማጺው ሕወሃት ደጋፊ እንደሆኑ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሐሰተኛ መረጃ እንደሚያሰራጩ ጠቅሶ የድርጅቱ የበላይ ቦርድ ምርመራ እንዲያደርግባቸው አቤቱታ ማቅረቡ ይሚታወስ ሲሆን ቦርዱ ይህን ያሳወቀው፣ በዶ/ር ቴዎድሮስ ሁለተኛ ዙር የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዕጩነት ላይ ለመወያየት ዛሬ በጀኔቫ ባደረገው ስብሰባ ላይ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ፣ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው እና ከቦርዱ አሠራር ውጭ እንደሆነ ኬንያዊው የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት 34 አባላት ላሉት ቦርድ የተናገሩ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከቦርዱ ይልቅ ሌላ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ቢመለከተው ይሻላል በማለት ያቀረቡትን ሃሳብ ቦርዱ ያለ አንዳች ተቃውሞ ተቀብሎታል በማለት ሮይተርስ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY