ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ህዋ ካመጠቀቻቸው ኹለት ሳተላይቶች የሚገኙ መረጃዎች አገልግሎት ላይ እየዋሉ አለመሆኑ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ ታኅሣሥ 10/2012 ያመጠቀቻት የመጀመሪያዋ ETRSS1 ሳተላይት እና ያንን ተከትሎ ከዓመት በኋላ የመጠቀችው ኹለተኛዋ ET-Smart-RSS›› ሳተላይት የሚልኩትን መረጃ ወስዶ፣ አገራዊ ጥቅም ላይ የሚያውል ተቋም አለመኖሩን ኢትዮጵያ ነገ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጣለች።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው፣ መረጃዎችን ከሳተላይቶች ተቀብሎ እና ተንትኖ መረጃ ቢያመርትም፣ መረጃዎች ለተፈለገው ዓላማ የሚጠቀም ተቋም የለም ተባለ።