ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከአልጀሪያው ፕረዚዳንት ጋር በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ 

ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከአልጀሪያው ፕረዚዳንት ጋር በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አብደል ፋታህ አልሲሲ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አልጀርስ ገብተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው የሕዳሴ ግድብ አሞላል እና አስተዳደር ዙሪያ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት መደረሱ ጠቃሚ እንደሆነ መስማማታቸው ተሰምቷል፡፡

የግብጹ ፕረዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ እንደገለጹት የግብጽ የውሃ ደህንነት ጉዳይ የአረብ ብሄራዊ የደህንነት አካል ስለሆነ የግብጽን የውሃ ደህንነት ማስጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተስማምተናል ብለዋል፡፡

የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አብዱል መጅድ ታቦን ግብጽ በህዳሴው ግድብ ፍትሃዊ አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የተሟላ ሥምምነት ላይ ለመድረስ የምታደርገውን ጥረት እንደሚያደንቁ መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡

የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላማምራ በኢትዮጵያ ሁለት ጊዜ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በቀጣይ ሊቀመንበር በምትሆንበት የዐረብ ሊግ ላይ ስለሕዳሴ ግድብ ሚዛናዊ ውይይት እንደምታደርግ መግለጻቸው ይታወሳል ሲል አል አይን ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY