ለ6 ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ

ለ6 ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ መሆኑን ገልጿል።

አክሎም ስጋቱን በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በመግለፅ ለ6 ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አሳውቋል።

በዚህም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የ6 ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ እንዲተላለፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል።

LEAVE A REPLY