ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱት 22 ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወስኗል።
በሰብአዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት ተከሳሾች የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ሰራተኞች የነበሩ ናቸው። በአንድ ዳኛ ተቃውሞ እና በሁለት ዳኞች አብላጫ ድምጽ ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው እንዲከላከሉ ብይን ተላልፏል።
የዋስትና መብታቸው ከተከበረላቸው ተከሳሾች መካከል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ም/ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን፣ የተቋሙ የጸረ ሽብር ወንጀሎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዑርጌ ይገኙበታል።
የዛሬውን ችሎት የኦ.ፌ.ኮ ፓርቲ አመራር የሆኑት ፖለቲከኛው ደጀኔ ጣፋ መታደማቸውም ታውቋል።