ህውሀት በአዲስ በከፈተው ጥቃት ምክንያት ቆቦ ላይ ተፈናቃዮች መስፈራቸውን ተሰምቷል

ህውሀት በአዲስ በከፈተው ጥቃት ምክንያት ቆቦ ላይ ተፈናቃዮች መስፈራቸውን ተሰምቷል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ከተፈናቃዮቹ መካከል ከበርካታ ወራት በኃላ ወደ መኖሪያ ቄያቸው ሀገር ሰላም ነው ብለው የተመለሱ ይገኙበታል ተብሏል።

አንድ ከዋጃ የተፈናቀሉ ግለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፥ አካባቢው ነፃ ወጣ ከተባለ በኃላ የመንግስት ሚዲያዎችም ገብተው ዘግበው እንደነበር ነገር ግን በታህሳስ 29 የህወሓት ታጣቂዎች ተመልሰው እንደገቡ ከዛ በኃላ ህፃናት፣ ሴቶች፣ እናቶች ተፈናቅለው ወደ ቆቦ መምጣታቸውን ገልጿል።

ህዝቡ ስቃይ ላይ ነው የሚዲያ ሽፋንም እያገኘ አይደለም ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል። ተፈናቃዮቹ በአሁን ሰዓት ከባድ የሚባል የምግብ እንዲሁም የአልባሳት እጥረት እንዳለባቸው ተነግሯል። የዋጃ ጥሙጋ ቀበሌ ዋና አስተዳደሪ ያሬድ አድማሱ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤ የህወሓት ኃይሎች ከታህሳስ መጨረሻ ጀምሮ ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ እና እንደአዲስ በከፈተው ጥቃት ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አሳውቀዋል።

ተፈናቃዮች በቆቦ ከተማ በሁለት ካምፕ ውስጥ ይገኛሉ። በሌላ በኩል፤ ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በትግራይ አዋሣኝ ቦታዎች አብአላ፣ በርሃሌ ኤሬብቲና መጋሌ በከፈተው አዲስ ጥቃት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሙሉ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሳውቀዋል

LEAVE A REPLY