አሜሪካ በአፋር ላይ አዲስ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዳሳሰባት ገለፀች

አሜሪካ በአፋር ላይ አዲስ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዳሳሰባት ገለፀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

ፕራይስ ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል።

ኔድ ፕራይስ በትላንትናው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል።

ይህ ውሳኔ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ፕራይስ፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም መጠየቃተውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቃል አቀባዩ፤ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY