ከጋምቤላ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 6 ህፃናት ታፍነው መወሰዳቸው ተገለፀ

ከጋምቤላ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 6 ህፃናት ታፍነው መወሰዳቸው ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት በተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሳቸውንና በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 6 ያክል ህፃናትን አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከደብብ ሱዳን የሚነሱት የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከአኝዋክ ዞን አምስት ህፃናትን አፍነው የወሰዱ ሲሆን ከኑዌር ዞን ደግሞ አንድ ህፃን አፍነው መውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡

እነኚሁ ታጣቂዎች አሁንም ቢሆን በኹለቱ ዞኖች ላይ የሚፈፅሙት ግድያ መቀጠሉን የተናገሩት ኦቶው ታጣቂዎቹ በአንድ ወር ውስጥም በ11 ሰዎች ላይ ግድያ መፈፀማቸውን፣ 4 ሰዎችን ማቁሰላቸውን እንዲሁም ከመቶ በላይ የቀንድ ከብቶችንም በኹለት ዙር መዝረፋቸውን ተናግረዋል፡፡

ያለውን ሁኔታ ለፌደራል መንግሰቱም ሆነ በጁባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቀናል፣ ያሉት ኦቶው ኦኮት ድርጊቱን ለማስቆም ከዚህ ቀደም ከደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች ጋር በስልክ ተነጋግናል፣ ነገር ግን በቀጣይ ከደቡብ ሱዳን ሃላፊዎች ጋር ፊት ለፊት በመገናኛት በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ሲሉም አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY