ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለወደሙ ተቋማት ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

ለተፈናቀሉ ወገኖችና ለወደሙ ተቋማት ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው ህወሃት ፈጽሞት በነበረው ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎቸና ውድመት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ110 ሚሊዮን ብር ባላይ ድጋፍ ማድረጉን የሰው ለሰው ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ቶሎሳ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ተፈጽሞባቸው የነበሩት የአማራና አፋር ክልሎች አካባቢዎች ነጻ እንደወጡ ድርጅቱ የድጋፍ ስራዎችን ማከናወን ጀምሯል።

በደብረ ብርሃንና ደሴ ከተሞች በትምህርት ቤትና የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለነበሩ ወገኖች የእለት ደራሽ እህል የህጻናት አልሚ ምግብ ለመልሶ መቋቋሚያ የሚውል ቁሳቁስ እና ሌሎችንም ድጋፎች አድርጓል ብለዋል።

በተመሳሳይ በአፋር ጭፍራ ተፈናቅለው ለሚገኙ ከ40ሺ በላይ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ገልጸው፤ በአጠቃላይ በሁለቱም ክልሎች ከ50 ሺህ 500 በላይ ዜጎች የአስቸኳይና ሌሎች ድጋፎች እንደተደረገላቸው ገልጸዋል።

በክልሎቹ በተደረገው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ከመራቤቴ እስከ ወልዲያ ድረስ ባሉ ስፍራዎች ውድመት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል።

LEAVE A REPLY