ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ግማሽ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ግማሽ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ግማሽ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም የእቅዱን 86 ነጥብ 4 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጿል።

ያለፈው ስድስት ወራት ለድርጅቱ አስቸጋሪ ወራት እንደነበሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።በስድስት ወራት ውስጥ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 60.8 ሚሊዮን ማድረሱን የገለጸ ሲሆን ይህም 20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በሀገሪቷ የነበረው የፀጥታ ሁኔታ እቅዱ ሙሉ በሙሉ እንዳይሳካ ተግዳሮት እንደነበር ገልፀው በሀገሪቱ ካሉ 8000 የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች 3471 የሚሆኑት አገልግሎት አቋርጠው እንደነበር ገልጸዋል።
በአማራ እና በአፋር ክልሎል ሙሉ በሙሉ ከአንድ ወር በላይ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ በገቢው ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩም ተገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት በአገልግሎት አሰጣጥ ማስተጓጎል ባይገጥመው የእቅዱን 97 ነጥብ 7 ማሳካት ይችል እንደነበር ፍሬሕይወት ጠቁመዋል

LEAVE A REPLY