ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግስት በቅርቡ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተናገሩት ንግግር ላይ ምላሽ የሰጠ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከ(ህወሓት) ጋር ድርድር አለመጀመሩን ዛሬ አስታወቀ።
የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሌሎች አካላት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ) ንግግር መጀመራቸውን አስታዉቀዉ እንደነበረና ዶክተር ደብረፅዮን የተጀመረው ንግግርም “ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያሳየ “መሆኑን መገለፃቸውን የሚታወስ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼቨለ) በሰጡት ቃል የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለሚያመጣ ለየትኛዉም አማራጭ በሩ ክፍት ነዉ ብለዋል።
ነገር ግን እስካሁን ድረስ ከህወሓት ጋር የተደረገ ንግግር የለም ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።