በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ከተሰማሩ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ከተሰማሩ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ምርት ላይ ከተሰማሩ የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች ጋር ምክክር መደረጉን ኢ/ር ተከለ ኡማ አስታወቁ።

በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ምርት ላይ ከተሰማሩ የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች ጋር ምክክር ማድረጋቸውን የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡

ከእንግሊዝ አምባሳደር ዶ/ር አላስታየር ምሲፋል እና ከአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊ ኒብሌት ጋር ነው ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለፁት፡፡

ውይይቱም በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ምርት ላይ በተሰማሩ የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ እና የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ በሰፊው የሚሳተፉበት መንገድ ላይም ኢንጂነር ታከለ ከአምባሳደሮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ነው የገለፁት።

LEAVE A REPLY