ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ልዩ ስሙ ገንዳ ሪራ በተባለ ስፍራ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎባ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ የደረሰ ሲሆን አደጋው ከደሎ መና ወደ ሮቤ ዶዘር እየጎተተ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ክሬን ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሮቤ ወደ ደሎ መና በመጓዝ ላይ ከነበረው የፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ 9 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህይወት ሲያልፍ ፥ በአራቱ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው ክሬኑን ሲያሽከረክር የነበረው ረዳት በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።
ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ጎባ ሪፌራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።