ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ጉብኝት ላይ ናቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ጉብኝት ላይ ናቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግስት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን እንደሚያከናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦረና ዞን በመገኘት ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት የጎበኙ ሲሆን በዞኑ የሚገኘውን የቦረና ከብት ዝርያ ማራቢያ እና ማስፋፊያ ማዕከልንም ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እያቀረበ ካለው የእለት ደራሽ ድጋፍ ባሻገር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

በቦረና ዞን እየተገነቡ ያሉ አነስተኛ ግድቦችን በአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም በዞኑ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ድርቅ የሚያስከትለውን ጉዳት በዘላቂነት መፍታት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዞኑ እያደረጉት ባለው ጉብኝት በያቤሎ ከተማ የተገነባውን ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትንም ተመልክተዋል።

LEAVE A REPLY