ባልደራስ ፖርቲ ፋኖ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም ሲል አስታወቀ

ባልደራስ ፖርቲ ፋኖ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም ሲል አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፋኖ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ነው በሚል ፍረጃ ወከባና ትንኮሳ እየተፈፀመበት ይገኛል ሲል ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ፓርቲው በመግለጫው ፋኖ በጊዜያዊነት ተሰባስቦ በአገር ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሙሉ በሙሉ እስከሚወገድ በዱር በገደሉ እየተሰማራ አካባቢውንና ሀገሩን ከጥቃት የሚከላከል ህዝባዊ ኃይል እንጂ፤ ቋሚ የሆነ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም” ብሏል።

የትንኮሳ ድርጊቱ ባልተጠናቀቀው ጦርነት በተጠንቀቅ የሚገኙትን ፋኖዎች ብቻ የሚነካ ሳይሆን፤ የመከላከያ፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላትን አንድነት፣ ሞራል እና ቅስም የሚሰብር ነው ብሏል ፓርቲው። በተጨማሪም ጫናውና ትንኮሳው ሕወሓትን፣ ኦነግ/ሸኔን እና ሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ቡድኖችን እና ኃይሎችን ተጠቃሚና ደስተኛ እንዲሁም ሞራላቸውን የሚያነቃቃ ነው” ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ገልጿል።

ከፌደራል መንግስቱ የመከላከያ ኃይል ውጭ ያሉትን ታጣቂዎች ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ከጦርነቱ በኋላ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚቀረፅ ፖሊሲ ሊወሰን ይገባል ብሏል።

LEAVE A REPLY