ቅዱስ ሲኖዶሱ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለመወያየት ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ተገለፀ

ቅዱስ ሲኖዶሱ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለመወያየት ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት በትናንትናው ዕለት የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ በመዋሉ ምክንያት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መገኘት አለመቻላቸው ተገልጿል።

ቢሆንም ግን ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በምክትል ከንቲባው የሚመራ የአመራር ቡድን በመንበረ ፓትሪያርኩ ፅ/ቤት ተገኝተው ከብፁአን የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጋር በቀጣይ ወይይት ስለሚደርግበት ሁኔታ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ ምክክሩም በመልካም ሁኔታ መካሄዱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

LEAVE A REPLY