ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጋራ ኮሚቴ ይቋቋማል ተባለ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት ማድረጋቸውን የከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት በማህበራዊ ገጹ አስፍሯል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመስቀል አደባባይ የባለቤትነት ጥያቄዎች የተነሳ በከተማ አስተዳደሩና በቤተ ክርስቲያኗ መካከል ውዝግቦች ተፈጥረዉ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የጋራ ኮሚቴው ከቤተ ክርስቲያኗ ቋሚ ሲኖዶስ እና ከከተማ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚዋቀር ሲሆን “ለጥያቄዎቹ የማያዳግም ምላሽ ይሰጣሉ” ተብሏል።