ኢሰመኮ በቁጥጥር ሥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠየቀ

ኢሰመኮ በቁጥጥር ሥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2014 ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይም በሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ እንዲነሳ መወሰኑን በበጎ መመልከቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ሁኔታ ወቅት ከአዋጁ አተገባበር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በድጋሚ አሳስቧል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት በቁጥጥር ሥር ውለው የተለቀቁ ሰዎችም በእስር ስለመቆየታቸው ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ወደ ሥራ መመለስ አለመቻልን ጨምሮ፤ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ባደረገው ክትትል መገንዘቡን ገልጿል፡፡

ስለሆነም ሰዎች በእስር የቆዩበትን ጊዜ ማስረጃና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች የመስጠቱን ሂደት እንዲፋጠንና ሰዎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ እንዲችሉ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡

LEAVE A REPLY