የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱን አስታወቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱን አስታወቀ

PM Netanyahu addressing the Ethiopian parliament

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡

ይህን ውሳኔ ተከትሎ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ መወሰኑን ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰሰጣጥ ሥርዓት እንዲያጠናቅቁም ምክር ቤቱ ወስኗል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጀምሮ እስር ላይ የሚገኙት ግለሰቦች እና ጋዜጠኞች በመንግሥት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም። በዚህም ጉዳይ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ጨምሮ ብዙዎች የክስ ሂደታቸው ሳይታይ እስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY