ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሚሽነሮች ምርጫ ሂደት ላይ የሚገኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ በህዝብ እንደራሴዎች በኩል አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ አካላት ጋር መደራደር ማለት አይደለም ሲል ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረዉ ጽሁፍ አመልክቷል።
በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደገለፁት “ጉዳዩ እኔ የምናገርበት ባይሆንም፤ ህወሓት ወታደራዊ ትጥቁን የሚፈታ እና በውስጡ የሚገኙ ወንጀለኞችን አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ በሀገርዊ ምክክሩ ሊሳተፍ ይችላል” ማለታቸው መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን
የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዓላማ እንደ ህገ መንግስት እና ሰንደቅ ዓላማ ባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፋፋይ ሀሳቦችን በሚያቀራርቡ ሀሳቦች መተካት ማስቻል ነው ሲል ፓርቲዉ በጽሁፉ ገልጿል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ 42 እጩ ኮሚሽነሮችን በህዝብ ድምፅ ሰብስቦ ይፋ ያደረገ ሲሆን የምክክር ኮሚሽኑ በ11 ኮሚሽነሮች እንደሚመራ መገልፁ ይታወሳል።