ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬ ልዩ ስብሰባው ዶ/ር መስፍን አርዓያ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል፡፡
ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ የ11 ኮሚሽነሮች ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል፡፡
እነርሱም ፕ/ሮ መስፍን አርዓያ ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌቱ አምባሳደር ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ ብሌን ገብረ መድህን ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ዘገየ አስፋው መላኩ ወልደ ማርያም አምባሳደር ማሕሙድ ዲሪር ሙሉጌታ አጎ ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ ሲሆኑ፤ የእጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት አፈ ጉባኤው ታገሰ ጫፎ ዕጩዎቹ የተመረጡበት መስፈርት ብዙኃነትን እና የፆታ ስብጥርን ከግምት ያስገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ኮሚሽነሮች ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ማገልገል እንደሚጠበቅባቸውም አፈ ጉባዔው አስረድተዋል።
ሹመቱ የፀደቀላቸው ኮሚሽነሮች በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመው ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አካታችና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በማሰብ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ ይታወቃል።