አሜሪካ የህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈፀሟቸው አሰቃቂ ድርጊት አሳስቦኛል አለቸች 

አሜሪካ የህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈፀሟቸው አሰቃቂ ድርጊት አሳስቦኛል አለቸች 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል በነሃሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ የተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶች በእጅጉን እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት መሰረት አድርጎ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም ሁሉም የታጠቁ የግጭቱ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ይቻል ዘንድ ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚል የጸና አቋም እንዳለውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አስታውቋል።

የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹ ሪፖርቶች አሁንም መውጣት መቀጠላቸው ግጭቱን በፍጥነት ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ሲልም በመግለጫው አሳስቧል።

ስለሆነም የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ የህይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታዎች ያለማቋረጥ እንዲሰጡ እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ለማሳሰብ በግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን ማሳተፍ እንቀጥላለን ሲልም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY