አድዋስ የተሰኘ ትያትር የፊታችን የካቲት 22 በወዳጅነት አደባባይ ለዕይታ ይቀርባል 

አድዋስ የተሰኘ ትያትር የፊታችን የካቲት 22 በወዳጅነት አደባባይ ለዕይታ ይቀርባል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአድዋ ድል ላይ የሚያጠነጥነው አድዋስ የተሰኘ ሙዚቃዊ ትያትር ለእይታ ሊበቃ ነው ተባለ። 126ኛው የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ እንደኾነ የተነገረው ትያትሩ የካቲት 22 ምሽት 12 ጀምሮ በወዳጅነት አደባባይ አንፊ ትያትር ይቀርባል ተብሏል እስከ 350 ሰዎችን ያሳተፈው ‘አድዋስ’ የተሰኘው ሙዚቃዊ ትያትር የአድዋ በአል ዋዜማ በወዳጅነት አደባባይ ለእይታ ሊበቃ እንደሆነ ተገልጿል።

በያሬድ ሹመቴ ተደርሶ በተስፋዬ እሸቱ ፕሮዲውስ የተደረገው ይህ ትያትር ባለቤትነቱ የጉዞ አድዋ ሲሆን ትላንት የካቲት 15/ 2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተዘጋጅቶ ያለቀው ይህ ሙዚቃዊ ትያትር እንደ አበበ ባልቻ፣ ተፈሪ ዓለሙ፣ ትግስት ግርማ እና አስመላሽ ታምራትን ጨምሮ ከህጻን እስከ አንጋፋ ተዋንያን እና 150 የዳንስ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

የቲያትሩ ደራሲ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ስለ ትያትሩ ሲገልጽ፣ “አድዋ የብዙ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ታሪክ ሲሆን ሃሳቡን ወደ ትያትር ለመቀየር ብዙ ጊዜ ፈጅቶብናል፤ ወደስራ የገባነው ጥር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ነው” ብሏል። ደራሲው ቲያትሩ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የ1 ወር ጊዜን ብቻ እንደወሰደም ተገልጿል።

ለትያትሩ ዝግጅትም የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር የ25,000 ብር እርዳታ እንደተደረገ ተገልጿል።  የቲያትሩ ፕሮዲውሰር የሆነው ተስፋዬ እሸቱ፣ “በፊልም ጽሁፍ እና በዝግጅት የላቀ ጥበብ የታየበት ነው፤ ቲያትሩ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ ሊያልቅ የቻለው እውነተኛ የአድዋ ልብ ባላቸው ሰዎች የተዋቀረ ቡድን መሰራቱ ነው፤ የ 350 ሰው ባህሪን ተረድቶ የተዋጣለት ስራ መሰራት መቻሉ እውነትም የትያትር ዝግጅቱ አባላት የአድዋ ልብ ያላቸው ስለመሆኑ ያሳያል ብሏል።

LEAVE A REPLY