ሩሲያ ከ70 የሚበልጡ የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን ገለፀች

ሩሲያ ከ70 የሚበልጡ የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን ገለፀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ  በሰጡት መግለጫ፥ ሞስኮ 11 የዓየር ሀይል ማዘዣዎችን ጨምሮ ከ70 የሚበልጡ በዩክሬን የሚገኙ ወታደራዊ ኢላማዎችን ማውደሟን አስታውቀዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን በመገንጠል ራሷን ነፃ አገር አድርጋ
ይህንን ተከትሎ በእስካሁኑ ወታደራዊ ዘመቻ በ74 የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማት ላይ የሩሲያ ዓየር ኃይል በፈፀመው ጥቃት መውደማቸውን ኢጎር ኮናሼንኮቭ አስታውቀዋል።

ከእነዚህ ውስጥም 11  የዓየር ኃይል ማዘዣዎች፣ 18 የዓየር መቃወሚያ የተተከለባቸው የራዳር ጣቢያዎች እና ሶስት የወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ማዕከላት እንደሚገኙበት ነው ያመለከቱት።

እንደ ቲ አር ቲ ዘገባ በኪየቭ አቅራቢያ የሚገኝ የዓየር ሀይል ማዘዣን ለመቆጣጠር የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ውጊያ በማድረግ ላይ ናቸው።

ተባብሶ የቀጠለው የዩክሬንና የራሺያ ጦርነት ሀያላን ሀገራት ከአባባሽ ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ መቅረባቸውን ይታወቃል።

ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና ቋሚ ተወካይ ዣንግ ጁን በተመድ 76ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩ፥አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ራሳቸውን በመቆጣጠር ውጥረቱን የሚያባብሱ እርምጃዎችን ከመውሰድ መቆጠብ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።የጀርመኑ መራሂተ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ሩሲያ በዩክሬን ላይ የሰነዘረችው ጥቃት በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን የሚጥስ ነው ሲሉ ኮንነዋል።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ፑቲን የደም መፋሰስን መንገድ መርጠዋል” ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ቃል ገብተዋል።

ዩክሬን በፊናዋ በኪየቭ አቅራቢያ ሲበር የነበረ አንድ የሩሲያን ሄሊኮፕተር እንዲሁም አምስት አውሮፕላኖችን መትቼ ጥያለሁ ብላለች።

ሞስኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር መሰረት እና የዶኔትስክ እና የሉጋንስክ ሪፐብሊኮች ከሩሲያ ጋር በገቡት የወዳጅነት ስምምነት መሰረት እየተፈፀመ መሆኑንም ነው ያስታወቀችው። አያይዘውም ዩክሬንን ፀረ- ሩሲያ ከሆኑ ናዚዎች ማፅዳትንም የወታደራዊ ዘመቻው ዓላማ እንደሆነ አመልክታለች።

LEAVE A REPLY