ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሕወሓት በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት ገንዘብ በመክፈል ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን መላኩ ተሰማ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ለቀበሌ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለጉምሩክ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት በአንድ ሰው ከ120 ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ በመክፈል፣ ከአንድ ሳምንት በፊት ከ60 በላይ ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን ማስወጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ሕወሓት ከአንድ ሳምንት በፊት ሠዎችን በሲኖትራክ ጭኖና በታጣቂዎቹ አሳጅቦ ወደ ሱዳን ያስወጣ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የወጡት እነዚህ ሠዎች ሱዳን ከሚገኘው “ሳምሪ” ከተባለው የሕወሓት ቡድን ጋር ሳይቀላቀሉ እንዳልቀሩ ተጠቁሟል፡፡