የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ላከች

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ላከች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሀገሪቱ 35 ቶን ምግብ የጫነ አውሮፕላን ወደ የትግራይ ክልል መዲና መቀሌ በዛሬው እለት መላኳን ገልጻለች፡፡

በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም አልረሽድ የተደረገው የምግብ እርዳታ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ ለመርዳት ነው ብለዋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ድጋፍ የምታደርገው ድጋፍ ለሚሹ ሀገራት ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ ባላት ቁርጠኝነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

የምግብ እጥረት ላለበት ህዝብ አስፈላጊ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ ኢምሬትስ ትሻለች ” ሲሉ የገለጹት አምባሳደሩ ” ይህ እርዳታ የተበረከተው ኢምሬትስ አስቸኳይ እርዳታ ለመፈልጉ ሀገራት ለመድረስ ባላት ቁርጠኝነት ነው ” ብለዋል፡፡

አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም ረሺድ ፥ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ባለፈው አመት 200 ቶን የአትክልት ዘይትን ጨምሮ 300 ቶን እርዳታ መቐለ ማድረሷን መግለፃቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY