ሩሲያ የሚሳየሎችና የከባድ መሳሪያ ጥቃቷን እንዳከፋችው የዩክሬን ሹሞች ተናገሩ

ሩሲያ የሚሳየሎችና የከባድ መሳሪያ ጥቃቷን እንዳከፋችው የዩክሬን ሹሞች ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  በተለይም 2ኛዋ የዩክሬን ታላቅ ከተማ ሐርኪቭ ዋነኛዋ የሩሲያ የከባድ መሳሪያ ሰለባ ነች ተብሏል፡፡ አንድ ከፍተኛ የጋዝ ማስተላለፊያ አውታር በመመታቱ ከባድ ቃጠሎ መቀስቀሱ ተሰምቷል፡፡

በርዕሠ ከተማዋ ኪየቭም የዩራኒየም ዝቃጩ መድፊያ ሥፍራ በሚሳየል መመታቱ ተሰምቷል፡፡ ያም ሆኖ የዩክሬይን ሹሞች ከተማዋን እስካሁን አልተነጠቅንም ብለዋል፡፡ ኪየቭም ባለፉት 4 ቀናት የሩሲያ ኃይሎች የጥቃት ዒላማ ብትሆንም የዩክሬይን መንግሥት ይዞታ ሆና መቀጠሏ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ቀጣዮቹ 24 ሰዓታት በጦርነቱ ሂደት እጅግ ወሳኝ ናቸው ሲሉ ተናግተናግሯል። ጀርመን ዩክሬንን የጦር መሳሪያ ልታስታጥቃት መሆኑን ቸሰምቷል፡፡ ምዕራብ አውሮፓዊቱ አገር ለዩክሬን በቀጥታ የጦር መሳሪያ እንደምትልክ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ተናግሯል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡ በዚህም መሰረት ጀርመን ለዩክሬይን 1000 ፀረ ታንክ መሳሪያዎች እና 500 በትከሻ ተጓጓዥ ስቲንገር ሚሳየሎችን ትልካለች ተብሏል፡፡

አውስትራሊያም በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በኩል ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ተሰናድታለች ተብሏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የ350 ሚሊዮን ዶላር የዋጋ ግምት ያላቸው የጦር መሳሪያዎች እንዲላኩ ማዘዛቸው ተሰምቷል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY