126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ ሩስያ እና አሜሪካ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ ሩስያ እና አሜሪካ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤፍጌኒ ተረክህን የዓደዋ ድል የኢትዮጵያ ህዝብ በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ፊት ለነጻነቱ እንዲበቃ የነጻነት እና የድፍረት ምልክት ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል። ለገለልተኛ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖሊሲዋ ጠንካራ ማበረታቻ ሆኖ አገልግሏል ብለዋል።

አምባሳደሩ ” የዓድዋ ጦርነት ያለምንም ማጋነን በባርነት የነበሩ አፍሪካዊያን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነፃ ለመውጣት ላደረጉት ትግል መሪ ኮከብ ነበር ሲሉ ነው የገለጹት።

ይህ ክስተት በሩሲያና በኢትዮጵያ ግንኙነት መመስረት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ የሚያስደስት ነው ” ያሉት አምባሳደሩ በጦርነቱ የቆሰሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ጦር ጀግኖችን ለማዳን የሩሲያ ሐኪሞች መርዳታቸውንም አስታውሰዋል።

ከዓድዋ ጦርነት በኋላ ብዙም ሳይቆይ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ለተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የአድዋ ድል የማዕዘን ድንጋይ መሆኑ አያጠያይቅም ነው ያሉት። በተተያያዘ ዜና አሜሪካ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

LEAVE A REPLY