የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ከቤት ውስጥ እስር እንዲፈቱ ተጠየቀ 

የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ከቤት ውስጥ እስር እንዲፈቱ ተጠየቀ 

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደረሰውን አቤቱታ ለማጣራት በላከው ቡድን አማካኝነት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የቤት ውስጥ እስረኛ መሆናቸውን እንዳረጋገጠ የገለፀ ሲሆን አቶ ዳውድ የሚገኙበት የቤት ውስጥ እስር ህጋዊ አግባብ የሌለው በመሆኑ የግለሰቡ የመንቀሳቀስ መብት እንዲከበር አሳስቧል።

አቤቱታውን ለማጣራት ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የአጣሪ ቡድኑ አባላት ሲሄዱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ሰራተኞች በር እንደተከፈተላቸው ቦርዱ አስታውቋል። አባላቱ ወደ ቤት እንዲገቡ ፈቃድ መጠየቁ፣ የያዙት ቦርሳ መፈተሹ እና የእጅ ስልካቸውን ይዘው እንዳይገቡ ተደርገው ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ተገናኝተዋል።

የአጣሪ ቡድኑ አባላት ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ባደረጉት ውይይት ከመጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከቤት እንዳይወጡ በግቢዉ በተመደቡ የታጠቁ ሰዎች ተከልክለዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የፓርቲ አመራሩ የሚገኙበት የቤት ውስጥ እስር በየትኛዉም የህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ የተመደበውን ጥበቃ በማንሳት የሊቀመንበሩን የመንቀሳቀስ መብት በማስከበር ለቦርዱ እንዲያሳውቁ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

LEAVE A REPLY