ባልደራስ ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩበት አስታወቀ

ባልደራስ ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩበት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ የካራማራ ድል በዓልን ለማክበር የተገኙ 25 የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን እና ደጋፊዎች እንዳሰረ ፓርቲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።

ባልደራስ ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ዛሬ የካቲት 26 የሚከበረውን የካራማራ የድል በዓል ለማክበር በድላችን ሀውልት የተገኘው የባልደራስ ቡድን ወደ አደባባዩ እንዳይገባ ከተደረገ በኋላ፣ የቡድኑ አባላት በሙሉ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።” ሲል አሳውቋል።

ፓሊስ ጣቢያ ከተወሰዱት መካከል፣ የፓርቲው ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ፣ ምክትል ሊቀመንበር ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ሥዩም እና አስካለ ደምሴ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ሌሎች ግን እንዳልተለቀቁ ፓርቲው ገልጧል።

ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮችና ደጋፊዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዳቸው ወደ “ድላችን ሐውልት ግቢ እንዳይገቡ ከከለከላቸው በኋላ እንደሆነ ተገልጧል። አባላቱ ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ መታሰራቸውን የገልፀዋል። ፓሊስ ለምን ይህን ርምጃ እንደወሰደ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ አልታወቀም።

LEAVE A REPLY