በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ የተከሰሱ እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈረደባቸዉ

በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ የተከሰሱ እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈረደባቸዉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. የወቅቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንንን ጨምሮ አመራሮችን እና የፀጥታ አካላትን በመግደል የተጠረጠሩ ተከሳቾች ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው የወንጀል ችሎት በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ግድያ ተከሰው በክስ መዝገቡ ከቀረቡትና ጥፋተኛ ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ ሶስት ተከሳሾች የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ሻምበል መማር ጌትነት፣ በላይሰው ሰፊነው እና ልቅናው ይሁኔ የተባሉ ተከሳሾች መሆናቸውንም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
ሌሎች 18 ተከሳሾች በ16 ዓመት ከ6 ወር እስራት፣ 2 ተከሳሾች በ15 ዓመት፣ 2 ተከሳሾች በ16 ዓመት፣ 4 ተከሳሾችን በ18 ዓመት እና 2 ተከሳሾችን በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የበየነ ሲሆን በጥቅሉ በዚህ የክስ መዝገብ 31 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ብያኔ ተላልፏል።

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እና ባህር ዳር ከተማዎች በተመሳሳይ ጊዜ በተፈፀመ ጥቃት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አምባቸው መኮንን፣ አማካሪያቸው እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምግባሩ ከበደ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እንዲሁም በጡረታ ላይ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊት አመራር ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ተገድለዋል።

የግድያ ሂደቱን መርቷል በሚል መንግስት ጀነራል አሳምነው ጽጌ ላይ እርምጃ መወሰዱን መሳወቁ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY