ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በማንነታቸው በሚደርስባቸው ጥቃት ከኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አቅራቢያ ተጠልለዋል።
300 ሺህ ያህል ዜጎች የዕለት ምግብ እና መጠለያ ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ የክልሉ ብዙኀን መገናኛ ዘግቧል።
የክልሉ ምግብ ዋስትና ቢሮ በየጊዜው ቁጥራቸው እየጨመረ ላሉት ተፈናቃዮቹ የዕለት ደራሽ የምግብ ዕርዳታ ለማቅረብ እጥረት እንደገጠመው ተናግሯል።
የክልሉ መንግሥት ለችግሩ ጊዜያዊ መፍትሄ የሚለው፣ ተፈናቃዮቹ የተፈናቀሉባቸው ክልሎች በሰላማዊ አካባቢዎች በጊዜያዊነት እንዲያሰፍሯቸው ነው መባሉም ተሰምቷል።